የጠፋብን ዕንቁ÷ ፍቅር

Bilderesultat for martin luther king

በዘመናት በበጎ ነገር ትውልድን ወደ ላቀ የነፃነትና የስኬት ማማ ያወጡ ሰዎች ፍፁም አፍቃሪዎች ነበሩ። ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር፣ ማህተማ ጋንዲ፣ ማዘር ቴሬዛ፣ ኔልሰን ማንዴላ፣ አብርሃም ሊክለንና የመሳሰሉት። እነዚህ የዘመናችን ከዋክብት የጨለማውን ዘመን በብርሃን የሰነጠቁ የፍቅር አማልክት የሆኑ ነግር ግን ሰዎች ነበሩ። በፍቅር ኖረው፣ ፍቅርን አንግሰው፣ ጥላቻን ከእግሮቻቸው ጫማ ስር ተጫምተው፣ በሰዎች መካከል ያለ ምንም ልዩነት አንድነትን፣ ነፃነትን፣ ፍትህንና እኩልነትን አቀንቅነዋል። አሳዳጆቻቸውን ያለምክንያት እየወደዱ፣ በጥላቻ ፋንታ ፍቅርን እየሰበኩ አምባገነኖችን ድል ነስተዋል፣ ህዝባቸውን ከባርነት ነፃ አውጥተዋል፣ የተጣሉትን ታድገዋል፣ በአጠቃላይ ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ መድህን ሆነው አልፈዋል። ከእነዚህ የዘመናት የፍቅር አማልክቶች የምንማረው ታላቁ ምስጢር ያለ ፍቅር አገርንና ትውልድን ነፃ ማውጣት የማይቻል መሆኑን ነው።
የእኛን አገር የአጭር ዘመን ታሩክ ብናይ እንኳ ደርግ ንጉሱን በጥላቻ አስወገደ፣ ወያኔ በተራው ደርግን በጥላቻ አስወገደ፣ ዛሬስ ወያኔን በጥላቻ ለማስወገድ መውተርተራችን ከፍቅር እጦት የመነጨ የአምባገነንነት አዙሪት ለመድገም መሆኑን አውቀን ይሆን? የትኛውም ለውጥ ከፍቅር ከጎደለ የተሟላ ለውጥ አይሆንም። እውነተኛ ለውጥ ለሚወዱንና ለሚደግፉን ብቻ ሳይሆን ለሚጠሉን፣ ለሚያሳድዱንና ሊያጠፉን ለሚፈልጉ ሁሉ ዋስትና የሚሰጥ ለውጥ መሆን አለበት። በደቡብ አፍሪካ የተደረገው ለውጥ ለዚህ ህያው ምስክር ነውና። የትኛውም የጥላቻ መንገድ ወደ ምንፈልገው የስኬት አደባባይ አያደርሰንም፣ የምንናፍቀውንም የነፃነት ቀን አያሳየንም።
በመሆኑም ፍቅርን አብዝተን እንናገር፣ በፍቅር እንገለጥ፣ የሚጠሉንን እንዲሁ እንውደድ፣ ለመጪው ትውልድ ተስፋ ፈንጣቂ የሆነ የፓለቲካ አስተሳሰብ እንላበስ። ያለ ፍቅር የመሩን ሁሉ መሪዎች ወደ ተሻለ የማህበረሰብ እድገት አላመጡንምና ከእነሱ መንገድ እንውጣ። የፍቅርን መንገድ እንከተል፣ ማንም ሊያሸንፈን አይችልምና። ስለዚህ ዛሬ የጠፋብንን እንቁ ፈልገን በምድራችን እናንግሰው። እሱም ሁላችንም የተፈጠርንበትና የምንኖርበት የፍቅር ኃይል ነው። ኃያሉ የጦር መሳሪያችን ፍቅር ብቻ ይሁን። ይህን ስናደርግ መላው ዓለም ከጎናችን ይቆማል፣ የሰው ዘር ሁሉ ሳይወድ በግድ ከጎናችን ይሰለፋል፣ አጋርነቱንም ያሳያል። ስለዚህ የጣልነውን እንቁ ፍቅርን እናንሳው፣ ፍቅር የእውነተኛ ማንነታችን መገለጫ ነውና በፍቅር እንነሳ።

ድልና አሸናፊነት ሁሌም ለአፍቃሪዎች ይሆናል!!
ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም!!
ፍቅር ለዘላለም አይሸነፍም!!
ፍቅር ሁሉን ያሸንፋል!!

About robiayansa

I learned that courage was not the absence of fear, but the triumph over it. The brave man is not he who does not feel afraid, but he who conquers that fear. Nelson Mandela Read more at: http://www.brainyquote.com/quotes/authors/n/nelson_mandela.html
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s